ኑር የቁርኣን ንባብ እና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል

እንኳን ወደ ኑር የቁርኣን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል በሰላም መጡ። ማዕከላችን በራሱ ኢንተርናሽናል አፕሊኬሸን ቁርኣንን በማስቀራት ከ ሶስት አመት በላይ ልምድ ያለው ሲሆን አሁንም አድማሱን በማስፋት በመላው ዓለም ለሚኖሩ የሰው ልጆች በሙሉ ባሉበት ቦታ ሁነው በተመችዎት ቀንና ሰአት ኑ የአላህን ቃል ቁርኣን ተማሩ ይላል። ኑር የቁርኣን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል።

ይመዝገቡ

500+

አሁን እየቀሩ ያሉ ተማሪዎች

80+

ወንድ እና ሴት ኡስታዞች

25+

ስታፍ ሠራተኞች

የማስተማር ስነ-ዘዴ

ኑር የቁርኣን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል የቂርኣት ሂደቱን የበለጠ ውጤታማ ለማድረግ በልዩ የማስተማሪያ ካሪኩለም በማዘጋጀትና የፈተና ፕሮግራም ፣ ወርሃዊ ዕቅድ እና ዕለታዊ የቂርኣት ሂደት ክትትል ማድረግ የሚቻልበትን ልዩ ጥናት ተደርጎ በትግበራ ላይ የሚገኝ ሲሆን ስድስት የቂርኣት ደረጃዎች አሉት። እነሱም ቃኢዳ፣ ደረጃ 1፣ ደረጃ2 ፣ ደረጃ 3 ፣ ደረጃ 4 ( እዚህ ላይ ቁርኣን ያኸትማሉ) ፣ ደረጃ 5 (ሙራጀኣ) ፣ ደረጃ 6 (ሂፍዝ) ። ሁሉም ተማሪዎች የማስተማሪያ ደረጃዎችን ተምረው ማዕከሉ ያስቀመጠውን የማለፊያ ነጥብ ማለፍ አለባቸው::

ከቁራኣን ማቅራት ባሻገር

1. ልዩ የክትትል ሂደት መስጠት መቻል

2. እንደ ቤተሰብ የሚወዱት እና የሚያማክሩት ማዕከል መሆኑ

3. የሀሳብ እና ጭንቀትዎ ተካፋይ መሆኑ

4. የትዕግስታችን መጨረሻ ትዕግስት መሆኑ

5. ተጨማሪ የተርቢያ እና የኪታብ ደርስ መስጠታችን

6. ልዩ የህይወት ከህሎት ስልጠና ፓኬጅ ማዘጋጀት እና ተማሪዎችን ማብቃታችን

ዓላማ

ዘመኑ ያፈራውን ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቁራኣንን ከንባብ እስከ ጽንሰ-ሀሳብ የተረዳ፤ በኢስላማዊ ስነ-ምግባር የታነጸ እና ከራሱ አልፎ ለሰው መትረፍ የሚችል የቁርኣን ትውልድ ማፍራት!!

ራዕይ

ቁርአንን እና ሐዲስን መሰረት ባደረገ አስተምህሮ ሰዎች ለተፈጠሩለት አላማ ተገዢ እንዲሆኑ በማድረግ ለፈጣሪያቸው ለአላህ (ሱ.ወ)ትክክለኛ ባርያዎች ሁነው ማየት!!

ተልዕኮ

የዓለም መድህን የሆነውን የአላህን ቃል (ቁርኣን) በተቀናጀ በተደራጀ እና ዘመኑን በዋጀ መልኩ ለመላው የሰው ልጆች ተደራሽ እንዲሆን መስራት!!

ኑር የቁርኣን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል የሚሰጣቸው አገልግሎቶች


1. የቁርኣን ንባብ መሰረት የሆነውን “ቃዒደቱ ኑራኒያ” ን ማስተማር

2. የቁርኣንን ንባብን እያዩ /በነዘር/ ማስተማር

3. ከቁርኣን ትምህርት ጎን ለጎን የተጅዊድ፣ የዐቂዳ፣ የሐዲስ፣ የፊቅህ፣ የሲራ እና የተርቢያ ኪታቦችን ማስተማር

4. የቁርኣን ሒፍዝ ፕሮግራም

5. ቁርኣን ላኸተሙ/ለጨረሱ/የኪታብ ትምህርት መስጠት

6. ከቁርኣን ጋር ተያያዝነት ባላቸው አጀንዳዎች ዙሪያ ጥናት እና ምርምር ማድረግ

7. በተርቢያ የታነፁ ስኬታማ ታዳጊዎችን ማፍራት

8. የስነ-ልቦና ምክር አገልግሎት
Register

ስለ እኛ

ኑር የቁርአን ንባብ እና እስላማዊ የጥናት ማዕከል በየትኛውም ሀገር የምትገኙ ሙስሊም ወንድም እና እህቶችን ባሉበት ቦታ ሆነው ቁርአን ተደራሽ እንዲሆንላቸው እየሰራን እንገኛለን:: የምናስተምረውም ከ አሊፍ እስከ ሂፍዝ ድረስ መማር ለሚፈልጉ ወንድሞች እና እህቶች ኡስታዞችን መድበን በማስተማር ላይ እንገኛለን...

Read More