ኑር የቁርኣን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል

ኑር የቁርኣን ንባብና ኢስላማዊ ጥናት ማዕከል ከተቋቋመበት 2012 ነሀሴ ወር ጀምሮ እስከ አሁኑ ሰዐት ድረስ ከ6000 በላይ ሙስሊም ወንድሞቻችን ና እህቶቻችንን ከትንሽ እስከ ትልቅ የዕድሜ ክልል ያሉ ሰዎችን ባሉበት ቦታ ሆነዉ የሚቻቸዉን ሰዓት ባሉበት ቦታ በራሱ አፕልኬሽን (Online) የአላህን ቃል ቁርኣን ባማረና ባጭር ጊዜ ዉጤታማ በሆነ መልኩ እያስቀራ ይገኛል ። እርስዎም የእድሉ ተጠቃሚ ይሁኑ።

ይመዝገቡ

ለቁርኣን ረፍዶ አያቅም!


- ረጅም አመት የማስተማር ልምድ ባላቸው ወንድ እና ሴት ኡስታዞች የሚያስተምር ማዕከል።

- በቂ የሴት እና የወንድ ኡስታዞች ያሉን ሲሆን የግል ኡስታዝ እና ተቆጣጣሪ መድበንልዎት የሚማሩበት ማዕከል ነው።

- ማዕከሉ የራሱ የሆነ ካሪኩለም ያለው ሲሆን ከቃኢደቱል ኑራንያ ወይም ከ አሊፍ ጀምሮ እስከ ሂፍዝ መቅራት ይችላሉ።

- ማዕከሉ በራሱ ስም ባዘጋጀው ኢንተርናሽናል አፕልኬሽን ታግዞ ኡስታዝዎ በአካል ሆኖ የሚያስቀራዎ እስኪመስልዎ በጥራት ይቀራሉ።

ለልጆቻችን


- ለልጆች ልዩ ተርቢያን በመስጠት የሚታወቀው ማዕከላችን አሁንም እርስዎንና ልጅዎን በጉጉት ይጠብቃል።

- በልጆች አያያዝ በሰለጠኑ ኡስታዞች እናስተምራለን።

- የለውጥ አለሙን የተገነዘቡ ኡስታዞችን በማፍራትና በማሰልጠን ማስተማራችን ልዩ ያደርገናል።

- ልዩ የህፃናት የስልጠና ፖኬጅ እንሰጣለን።

- በማንኛውም እድሜ ክልል ላሉ ሁሉ እናስተምራለን።

በታላላቅ መሻይኾች የቦርድ አመራርነት የሚመራ


- ማዕከላችን የቁርኣን ማዕከል እንደመሆኑ መጠን በማንኛውም የቂርኣት ሂደት ጉዳዮችን በሙሉ ክትትልና ቁጥጥር ለማድረግ በሀገራችን ደረጃ ታላላቅ መሻይኾችን የቦርድ አመራር በማድረግ ስድስት ኡስታዞችንና መሻይኾችን የቦርድ አማካሪ አድርጎ በመስራት ላይ ይገኛል።

- የቦርድ አማካሪው አካል የማዕከሉን ስራዎች ከማማከር በተጨማሪ ቋሚ የዳእዋ ፕሮግራም በመያዝ ለተማሪዎቹ ሳምንታዊ የዳዕዋ ትምህርት ይሰጣሉ።

የክፍያ ሁኔታ

ውድ ተማሪዎች እኛ ለቁርኣን አናስከፍልም እናንተም ለቁርኣን መክፈል አትችሉም ቁርኣንን በገንዘብ አንለካም አይለካምም።   

ክፍያው በሰአቱ ሌላ ስራ ከሚሰራበት ቁርኣን ይቀራበት ዱንያዊ ጉዳዮችን እንሸፍን ነው።       

24 ሰአት ጊዜያቸውን ቁርኣን ለማስቀራት የሰጡ በቂ ወንድ እና ሴት ኡስታዞች አሉን ክፍያችን ለኡስታዞቻችን እና ለቢሮ ሰራተኞች ለዱኒያዊ ጉዳዮቻቸው በማዋል ቁራኣንን ማስቀጠል ነው።

ከሰማንያ በላይ ወንድ እና ሴት ስታፍ ሰራተኞች ያሉን ሲሆን በማንኛውም ሰአት ተማሪን ለማስተናገድ ዝግጁ ሁነው የሚጠብቁ ናቸው።

4G ኔትዎርክ በመጠቀም የመማር ማስተማር ሂደቱን ያዘመነ ማዕከል ነው።